የባለአክሲዮኖች 6ኛ መደበኛ እና 2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ


የባለአክሲዮኖች 6ኛ መደበኛ እና 2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ

የአክሲዮን ማህበሩ ስም የምስራች ማይክሮ ፋይናንስ ኢማ
የአክሲዮን ማህበሩ አይነት ፡ በማይክሮ ፋይናንስ ስራ የተሰማራ
የማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ (ካፒታል) ► 23,934,000.00
የማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ (ካፒታል) ► 23,934,000.00
የዋና መስሪያ ቤት አድራሻ ፦ ከተማ አ/አ፣ ክ/ከ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር 233
የማይክሮፋይናንስ ስራ ፈቃድ ቁጥር ME/045/2018
የንግድ ምዝገባ ቁጥር፦ NL/AA/3/0012777/2010


የምሥራች ማይክሮፋይናንስ ኢማ የባለአክሲዮኖች 6ኛ መደበኛ እና 2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ቅዳሜ ታህሳስ 19 ቀን 2017 ዓ.ም፤ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በኢት/ወ/ቤ/ክ/መ/ኢየሱስ ሴምናሪየም የስብሰባ አዳራሽ ስለሚካሄድ ፣ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተጠቀስው ቀንና ሰዓት በጉባዔው ላይ እንድትገኙ የዲረክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የ6ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

1 የጉባዔውን አጀንዳዎች ማጽደቅ፣
2. አዳዲስ ባለአክስዮኖችን መቀበል፤
3 የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርትን ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
4. የውጭ አድተር ሪፖርትን ማዳመጥ፣ እና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
5. ከ2017-2019 የሚያገለግሉ የውጭ ኦዲተሮችን መምረጥ እና ክፍያቸውን መወሰን፣
6. ከ2017-2019 ዓም የሚያገለግሉ የቦርድ አባላትን መምረጥ እና አበላቸውን መወሰን፣
7. የ2016 ዓ.ም አመታዊ ትርፍ ክፍፍል ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
8 የጉባኤውን ቃለጉባኤ ማጽደቅ፤

የ2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አጀንዳዎች

1. የጉባዔውን አጀንዳዎች ማጽደቅ
2. ተሽጦ ያላለቁ የተቋሙ አክሲዮኖች ተሽጦ ማለቅ በምችሉበት ሁነታ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
3 የጉባኤውን ቃለጉባኤ ማጽደቅ፤

ስለሆነም ነባርና አዳዲስ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወክሎች ማንነታችውን የሚገልጽ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ እና በህጋዊ አካል የተረጋገጠ የውክልና ማስረጃ ዋናውንና ኮፒውን በመያዝ ስብሰባው ላይ እንድትገኙ በአክብሮት ይጋብዛል፡፡

የዲሬክተሮች ቦርድ

የምሥራች ማይክሮፋይናንስ ኢማ


ምላሽ ይስጡ